ከልባችን ስር ነሽ ዓለማያ

የትዝታችን መነሻ የእኛነታችን መሠረት
ዓለማያ ነፋሻዋ ሁሉ አቀፍ የግብርና ት/ቤት
በአንች ጉያ ዕቅፍ ላይ ሆኖ የተማረ ተማሪ
ኋላም የሆኑ የእርሻ ትምህርት አስተማሪ
ሌላው ዶክተር ፕሮፌሰር ያፈራሽ ተመራማሪ
አንረሳሽም እንወድሻለን ከልባችን ከውስጥ
ምንም እንኳን ጊዜው ቢርቅ ቢሮጥ
አለሽ ከልባችን ሥር ሆነሽ አብሪ ጌጥ
ትሆኛለሽ በልጆችሽ ዕንቁ የዕንቁዎች ፈርጥ፡፡
ተመዘገብሁ በቃ ዓለማያ ለትዝታ
አንችን ላገኝ ልከፍልሽ ያለብኝን ውለታ
ነገ አይደለም ዛሬ ሳይመሽ ሳይሆን ማታ፡፡
ሁልጊዜ ነው ማስብሽ ከውስጥ ልቤ ጉያ
አልረሳሽም በሕይወቴ የእኔ ነሽ ዓለማያ፡፡
=====================
ከጋሻው ሽባባው (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፀሐፊ)

Scroll to Top
bigwin777